Skip to content

የባትሪ እና የኃይል ችግሮች

ይህ መመሪያ በእርስዎ ውሪ ነካ ላይ የሚያጋጥሙ የተለመዱ የባትሪ እና የኃይል ነክ ችግሮችን ለመለየትና ለመፍታት ይረዳዎታል።


የተለመዱ የባትሪ ችግሮች

መሣሪያው አልበራም ካለ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • ባትሪው ሙሉ በሙሉ ተሟጧል።
  • ቻርጀሩ በትክክል አልተገናኘም።
  • መሣሪያው በእንቅልፍ ሁኔታ (sleep mode) ላይ ነው።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ቻርጀሩን በመሣሪያው ላይ ካለው የቻርጅ ማድረጊያ ቀዳዳ (ቁጥር 4) ጋር ያገናኙ።
  2. ባትሪው በቂ ኃይል እስኪያገኝ ድረስ ከ5–10 ደቂቃ ይጠብቁ።
  3. መሣሪያውን ለማብራት የመካከለኛውን ቁልፍ (ቁልፍ 7) ተጭነው ይቆዩ።
  4. መሣሪያው አሁንም አልበራ ካለ፣ ቻርጀሩ እና ኬብሉ (cable) ያልተጎዱ መሆኑን ያረጋግጡ።

ባትሪ በፍጥነት የሚያልቅ ከሆነ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • የስክሪኑ ብርሃን በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ተደርጓል።
  • መሣሪያው ጥቅም ላይ በማይውልበት ጊዜ ሳይጠፋ መቆየቱ።
  • ባትሪው ያረጀ ወይም የተበላሸ መሆኑ።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ማስተካከያ (Settings) > ስክሪን (Screen) ውስጥ የስክሪኑን የብርሃን መጠን ይቀንሱ።
  2. ማስተካከያ (Settings) > ስክሪን (Screen) ውስጥ አጭር የስክሪን መቆለፊያ ሰዓት ያዋቅሩ።
  3. መሣሪያው አገልግሎት ላይ በማይውልበት ጊዜ ወደ እንቅልፍ ሁኔታ እንዲቀየር ያድርጉ (የግራ ቁልፍን ተጭነው ይቆዩ)።
  4. ችግሩ ካልተቀረፈ፣ ባትሪው መቀየር ሊያስፈልገው ስለሚችል የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ።

መሣሪያው ሳይታሰብ በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ከሆነ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • የባትሪው ኃይል በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
  • መሣሪያው ከመጠን በላይ ሙቋል።
  • የሶፍትዌር ስህተት (software error)።

ምን መደረግ አለበት?

  1. በሁኔታ ባር (status bar) ላይ የባትሪውን ደረጃ ይፈትሹ።
  2. ባትሪው ዝቅተኛ ከሆነ፣ ወዲያውኑ ቻርጀሩን ይሰኩት።
  3. መሣሪያው በጣም ከሞቀ እንዲቀዘቅዝ ይተዉት።
  4. መሣሪያውን መልሰው ያስጀምሩት (Restart ያድርጉት)።
  5. ችግሩ ከቀጠለ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ።

ቻርጅ የሚያደርገው በጣም ቀርፋፋ ከሆነ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • እውቅና ያልተሰጠው ቻርጀር ወይም ኬብል መጠቀም።
  • ቻርጅ እየተደረገ መሣሪያውን በከፍተኛ ሁኔታ መጠቀም (ለምሳሌ ማተም/ፕሪንት ማድረግ)።
  • የቻርጅ ማድረጊያ ቀዳዳው መቆሸሽ ወይም መጎዳት።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ከመሣሪያው ጋር አብሮ የመጣውን ቻርጀር ብቻ ይጠቀሙ።
  2. ቻርጅ በሚያደርግበት ጊዜ ማተም (printing) ያቁሙ።
  3. የቻርጅ ማድረጊያ ቀዳዳውን ከቆሻሻ ወይም ፍርፋሪ የጠራ መሆኑን ይፈትሹ – ካስፈለገም በቀስታ ያጽዱት።

የባትሪው መቶኛ በድንገት የሚዘል ወይም 0% ላይ የሚቆም ከሆነ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • ባትሪው ብልሽት አለበት።

ምን መደረግ አለበት?

  1. መሣሪያውን ሙሉ በሙሉ 100% ቻርጅ ያድርጉት።
  2. መሣሪያውን በራሱ ጊዜ እስኪጠፋ ድረስ ይጠቀሙበት።
  3. ምንም ሳይቋረጥ መልሰው ወደ 100% ቻርጅ ያድርጉት።
  4. አሁን የመቶኛ ደረጃው በትክክል እያነበበ መሆኑን ያረጋግጡ።

ቻርጀሩን መለየት ካልቻለ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • ቻርጀሩ በትክክል አልተሰካም።
  • ቻርጀሩ ወይም ኬብሉ ተጎድቷል።
  • የቻርጅ ማድረጊያ ቀዳዳው ብልሽት አለበት።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ቻርጀሩን ነቅለው እንደገና ይሰኩት።
  2. ሌላ የግድግዳ ሶኬት ይሞክሩ።
  3. ኬብሉ ላይ ጉዳት አለመኖሩን ይፈትሹ።
  4. ሌላ ቻርጀር (ካለ) ይሞክሩ።
  5. ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ካልሠሩ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ።

የባትሪ ደኅንነት

ማስጠንቀቂያ መግለጫ
ከመጠን በላይ ቻርጅ አያድርጉ መሣሪያው ሙሉ በሙሉ ቻርጅ ሆኖ ሲያበቃ ቻርጀሩን ይንቀሉ።
ከከፍተኛ ሙቀት ይከላከሉ መሣሪያውን በቀጥታ የፀሐይ ብርሃን በሚያርፍበት ቦታ ወይም በሙቅ መኪና ውስጥ አይተዉት።
እውቅና ያላቸውን ቻርጀሮች ይጠቀሙ ከመሣሪያው ጋር አብሮ የተሰጠውን ቻርጀር ብቻ ይጠቀሙ።
አይፍቱት ባትሪውን በራስዎ ለመንቀል ወይም ለመቀየር አይሞክሩ – ይህ የዋስትና መብትዎን የሚያሳጣ ከመሆኑም በላይ አደገኛ ሊሆን ይችላል።

የባትሪ ሁኔታ ምልክቶች

እዚህ ጋር ይመልከቱ የባትሪ ሁኔታ


አሁንም ችግሮች ካጋጠሞት?

ከላይ የተጠቀሱትን እርምጃዎች በሙሉ ሞክረው ችግሩ ካልተቀረፈ፣ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ፦

  • ኢሜይል፦ info@adcethiopia.com
  • ስልክ፦ +251 93 007 6905

እባክዎ የመሣሪያዎን መለያ (Device ID) አስቀድመው ያዘጋጁ (በ ማስተካከያ [Settings] > የመሣሪያ መረጃ [Device Info] ውስጥ ይገኛል)።


የሚቀጥሉ እርምጃዎች

ወደ ሌሎች የዕክሎች መፍቻ መመሪያዎች ይቀጥሉ።

➡️ ወደ ዕክሎች መፍቻ ይመለሱ

Battery & Power Problems

This guide helps you diagnose and fix common battery and power-related issues with your Wurii NEKA.


Common Battery Issues

Device Does Not Turn On

Possible Causes:

  • Battery is completely drained.
  • Charger is not connected properly.
  • The device is in sleep mode.

What to Do:

  1. Connect the charger to the charging port (number 4).
  2. Wait 5–10 minutes for the battery to get enough charge.
  3. Press and hold the middle key (button 7) to turn the device on.
  4. If the device still does not turn on, check the charger and cable for damage.

Battery Drains Quickly

Possible Causes:

  • Screen brightness is set too high.
  • The device is left on when not in use.
  • The printer is on and waiting.
  • GPRS is active when WiFi could be used.
  • The battery is old or damaged.

What to Do:

  1. Reduce screen brightness in Settings > Screen.
  2. Set a shorter screen lock timeout in Settings > Screen.
  3. Put the device to sleep when not in use (press and hold the left key).
  4. Use WiFi instead of GPRS for data transfers (WiFi uses less power).
  5. If the problem persists, the battery may need replacement – contact support.

Device Shuts Down Unexpectedly

Possible Causes:

  • Battery is critically low.
  • The device is overheating.
  • Software error.

What to Do:

  1. Check the battery level in the status bar.
  2. If the battery is low, plug in the charger immediately.
  3. Allow the device to cool down if it feels hot.
  4. Restart the device.
  5. If the problem continues, contact support.

Charging Is Slow

Possible Causes:

  • Using a non‑approved charger or cable.
  • Charging while using the device heavily (e.g., printing).
  • The charger port is dirty or damaged.

What to Do:

  1. Use only the charger that came with the device.
  2. Stop printing while charging.
  3. Check the charging port for dirt or debris – clean gently if needed.

Battery Percentage Jumps or Stays at 0%

Possible Causes:

  • The battery is faulty.

What to Do:

  1. Fully charge the device to 100%.
  2. Use the device until it turns off automatically.
  3. Charge it back to 100% without interruption.
  4. Check if the percentage now reads correctly.

Charger Not Detected

Possible Causes:

  • Charger is not plugged in properly.
  • Charger or cable is damaged.
  • The charging port is faulty.

What to Do:

  1. Unplug and re‑plug the charger.
  2. Try a different wall socket.
  3. Inspect the cable for damage.
  4. Try a different charger (if available).
  5. If none of these work, contact support.

Battery Safety

Warning Description
Do not overcharge Unplug the charger once the device is fully charged.
Avoid extreme heat Do not leave the device in direct sunlight or in a hot car.
Use approved chargers Only use the charger supplied with the device.
Do not disassemble Do not attempt to remove or replace the battery yourself – this voids the warranty and may be dangerous.

Battery Status Icons

Refere here Battery Status


Still Having Problems?

If you have tried all the steps above and the issue persists, contact support:

  • Email: info@adcethiopia.com
  • Phone: +251 93 007 6905

Please have your Device ID ready (found in Settings > Device Info).


Next Steps

Continue to other troubleshooting guides.

➡️ Return to Troubleshooting