Skip to content

የቁልፍ ሰሌዳ አጠቃቀም

የነካ የቁልፍ ሰሌዳ መረጃን በብቃት ለማስገባት ተሻሽሎ የተሰራ ነው። ይህ መመሪያ ቁጥሮችን፣ የእንግሊዝኛ ጽሑፎችን እና የአማርኛ ፊደላትን ለማስገባት የሚያገለግሉትን የተለያዩ የቁልፍ ሰሌዳ ሁነታዎች (modes) እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያብራራል።


የቁልፍ ሰሌዳው አጠቃላይ ገጽታ

የቁልፍ ሰሌዳው ለመተየብ በጋራ የሚሠሩ አምስት ዋና ዋና ቁልፎች (ከቁጥር 5 እስከ 9) አሉት። የቁልፍ ሰሌዳው ሦስት ዓይነት መረጃ ማስገቢያ ሁነታዎች አሉት፦

ሁነታ (Mode) ለአገልግሎት የሚውለው
Numeric (የቁጥር) ቁጥሮችን፣ ዋጋዎችን፣ መጠኖችን እና የገንዘብ ልኮችን ለማስገባት።
Alphanumeric (የፊደልና ቁጥር) የእንግሊዝኛ ጽሑፎችን፣ የእቃዎች ስም እና የኢሜይል አድራሻዎችን ለማስገባት።
Amharic (የአማርኛ) የአማርኛ ጽሑፎችን፣ ስሞችን እና አድራሻዎችን ለማስገባት።

የማስገቢያ ሁነታዎችን መቀያየር

ፈንክሽን ቁልፍን (ቁልፍ 9) ተጭነው በመያዝ ሁነታዎችን መቀያየር ይችላሉ።

  • ቁጥር – ቁጥሮችን ለማስገባት የሚያገለግል መደበኛ (default) ሁነታ ነው።
  • እንግሊዝኛ ፊደላት/ቁጥር – የእንግሊዝኛ ፊደላትን እና ምልክቶችን ለማስገባት።
  • አማርኛ – የአማርኛ ፊደላትን ለማስገባት።

በስክሪኑ ግርጌ ላይ የሚታየው የመጠቆሚያ ምልክት (cursor icon) በአሁኑ ሰዓት በየትኛው ሁነታ ላይ እንዳሉ ያሳያል፦

ምልክት (Icon) ሁነታ (Mode)
curser የቁጥር (Numeric)
curser የእንግሊዝኛ ትናንሽ ፊደላት (Alphanumeric (lowercase))
curser የእንግሊዝኛ ታላላቅ ፊደላት (Alphanumeric (uppercase))
curser አማርኛ (Amharic)

የቁጥር ሁነታ (Numeric Mode - መደበኛ)

ይህንን ሁነታ ቁጥሮችን፣ ዋጋዎችን እና መጠኖችን ለማስገባት ይጠቀሙበት።

ቁጥሮችን ማስገባት

  • መጻፍ የሚፈልጉትን ቁጥር የያዘውን ቁልፍ ይጫኑ።
  • ቁልፎቹ ከ1–9 እና 0 ባሉ ቁጥሮች ተለይተው ተቀምጠዋል።

አስርዮሽ (Decimal) ማስገባት

  • የአስርዮሽ ነጥብ (.) ለማስገባት፣ ነጥቡ እስኪታይ ድረስ ቁልፍ 6ን ሁለት ጊዜ ይጫኑ።
  • በቁጥር ሁነታ ማስገባት የሚችሉት አንድ የአስርዮሽ ነጥብ ብቻ ነው።

የኮማ (Comma) አቀራረብ

  • ትላልቅ ቁጥሮች በራስ-ሰር በኮማ ተለይተው ይቀመጣሉ (ለምሳሌ፦ 10,000)።

የፊደልና ቁጥር ሁነታ

ይህንን ሁነታ የእንግሊዝኛ ጽሑፎችን፣ የዕቃዎች ስም፣ የደንበኛ ስም እና የኢሜይል አድራሻዎችን ለማስገባት ይጠቀሙበት።

ፊደላትን ማስገባት

እያንዳንዱ ቁልፍ ከአንድ በላይ ፊደላትን ይዟል። በፊደላቱ መካከል ለመዘዋወር ቁልፉን በተደጋጋሚ ይጫኑ።

የቁልፍ ሰሌዳ ቁጥር ፊደላት እና ምልክቶች
1 1 . @ ? ! * # % + - : " / \
2 a b c 2
3 d e f 3
4 g h i 4
5 j k l 5
6 m n o 6
7 p q r s 7
8 t u v 8
9 w x y z 9
0 space 0 _

ምሳሌ፦ "Apple" ብሎ ለመጻፍ

  1. a ለማግኘት ቁልፍ 2ን አንድ ጊዜ ይጫኑ።
  2. p ለማግኘት ቁልፍ 7ን መደጋገሚያ ምልክቱ እስኪመጣ ድረስ ይጫኑ።
  3. ሁለተኛውን p ለማግኘት ቁልፍ 7ን ድጋሚ በተመሳሳይ መልኩ ይጫኑ።
  4. l ለማግኘት ቁልፍ 5ን በተደጋጋሚ ይጫኑ።
  5. e ለማግኘት ቁልፍ 3ን በተደጋጋሚ ይጫኑ።

የፊደል መጠን መቀያየሪያ

  • የፋንክሽን ቁልፍን (ቁልፍ 9) በአጭሩ በመጫን የታላላቅ (uppercase) እና የትናንሽ (lowercase) ፊደላት ሁነታን ማፈራረቅ ይችላሉ።
  • ታላላቅ/Caps Lock በርቶ በሚሆንበት ጊዜ የመጠቆሚያው ምልክት A (ታላቅ ፊደል) ያሳያል።

ልዩ ምልክቶች

  • በልዩ ምልክቶች መካከል ለመዘዋወር ቁልፍ 1ን በተደጋጋሚ ይጫኑ፦
  • ., @, ,, ?, !, *, #, %, +, -, :, ", /

የአማርኛ ሁነታ

ይህንን ሁነታ የአማርኛ ጽሑፎችን፣ የደንበኛ ስሞችን እና አድራሻዎችን ለማስገባት ይጠቀሙበት።

የአማርኛ ፊደላትን ማስገባት

እያንዳንዱ ቁልፍ መነሻ (ግዕዝ) ፊደል አለው። በፊደሉ ዘሮች መካከል ለመዘዋወር ቁልፉን በተደጋጋሚ ይጫኑ።

ቁልፍ መነሻ ፊደላት (Base Characters)
2 ሀ ለ መ
3 ረ ሰ ሸ ቀ
4 በ ተ ቸ ነ
5 ኘ አ ከ
6 ወ ዘ ዠ
7 የ ደ ጀ ገ
8 ጠ ጨ ጰ
9 ፀ ፈ ፐ ቨ
0 space _ ፩ ፲ ፻ ፼

የፊደል ዘሮች/ቤተሰቦች

አንድን የአማርኛ መነሻ ፊደል ከመረጡ በኋላ፣ የፊደሉን ዘሮች (ካዕብ፣ ሳልስ፣ ራብዕ...) ለመቀያየር የግራ (8) እና የቀኝ (6) ቁልፎችን መጠቀም ይችላሉ።

ለምሳሌ፦ የሚለውን ከተየቡ በኋላ፣ ወደ ለመቀየር የቀኝ (6) ቁልፍን መጫን ይችላሉ።

  • ፊደሉን ለማረጋገጥ የመካከለኛውን ቁልፍ (ቁልፍ 7) ይጫኑ።
  • ለመሰረዝ እና ወደ ቀደመው ፊደል ለመመለስ የኋሊት ማጥፊያ (ቁልፍ 5)ን ይጫኑ።

ምሳሌ፦ "ሰላም" ብሎ ለመተየብ

  1. ለማግኘት ቁልፍ 3ን በተደጋጋሚ ይጫኑ።
  2. ለማግኘት ቁልፍ 2ን በተደጋጋሚ ይጫኑ፤ ከዚያም በ ዘሮች መካከል ለመዘዋወር የግራና ቀኝ ቁልፎችን በመጠቀም ወደ ይሂዱና የመካከለኛውን (enter) ቁልፍ ይጫኑ።
  3. ለማግኘት ቁልፍ 2ን በተደጋጋሚ ይጫኑ፤ ከዚያም በ ዘሮች መካከል ለመዘዋወር የግራና ቀኝ ቁልፎችን በመጠቀም ወደ ይሂዱና የመካከለኛውን (enter) ቁልፍ ይጫኑ።

ጽሑፍን ማስተካከል

ተግባር እንዴት እንደሚከናወን
የመጨረሻውን ፊደል ማጥፋት የኋሊት ማጥፊያ (ቁልፍ 5)ን በአጭሩ ይጫኑ።
ሙሉውን ጽሑፍ ማጥፋት የኋሊት ማጥፊያ (ቁልፍ 5)ን ተጭነው ይቆዩ።
ከማንኛውም መረጃ ማስገቢያ ስክሪን መውጣት የግራ ቁልፍ (ቁልፍ 8)ን ተጭነው ይቆዩ።

አጫጭር መንገዶችን (Shortcuts) መጠቀም

መረጃ በሚያስገቡበት ወቅት፦

  • ልዩ ተግባራትን (ለምሳሌ፦ ቅናሽ፣ አዲስ ድምር) በፍጥነት ለመክፈት ፋንክሽን (9) ቁልፍን ተጭነው ከዚያ አንድ ቁጥር ይጫኑ።
  • በማውጫዎች (menus) ውስጥ እያሉ፣ በቀጥታ ወደ ፈለጉት የማውጫ አማራጭ ለመዝለል ፈንክሽን (9) ቁልፍን ተጭነው ከዚያ የሚፈልጉትን ቁጥር ይጫኑ።

ተጨማሪ ጠቃሚ ምክሮች

  • በአንድ ቁልፍ መዘዋወር – በአንድ ቁልፍ ላይ ያሉትን የተለያዩ ፊደላት ለመቀየር ያንኑ ቁልፍ በተደጋጋሚ ይጫኑ።
  • ተጭኖ መቆየት (Long press) – አንድን ቁልፍ ቆየት አድርጎ መጫን ልዩ ተግባር ያከናውናል (ለምሳሌ፦ ማጥፊያን ተጭኖ መቆየት ሙሉውን ጽሑፍ ያጠፋል)።
  • የመጠቆሚያ ምልክት (Cursor icon) – በየትኛው የቁልፍ ሰሌዳ ሁነታ ላይ እንዳሉ ያሳያል።
  • ከፍተኛው የፊደል ገደብ – የሚፈቀደው ከፍተኛው የፊደል ወይም የቁጥር መጠን ላይ ሲደርሱ የመረጃ ማስገቢያ ሳጥኑ ወደ አረንጓዴ ቀለም ይቀየራል።

የሚቀጥሉ እርምጃዎች

የNFC ካርዶችን እንዴት ማንበብ እንደሚችሉ ይማሩ።

➡️ ወደ ካርዶችን ማንበብ ይቀጥሉ

Keypad Usage

The Wurii NEKA keypad is designed for efficient data entry. This guide explains how to use the different keypad modes for entering numbers, text, and Amharic characters.


Keypad Overview

The keypad has five main buttons (numbers 5–9) that work together to let you type. The keypad has three input modes:

Mode Use For
Numeric Entering numbers, prices, quantities, and amounts.
Alphanumeric Entering text (English), item names, and email addresses.
Amharic Entering Amharic text, names, and addresses.

Switching Keypad Modes

You can switch between modes by pressing and holding the Function key (button 9).

  • Numeric – the default mode for entering numbers.
  • Alphanumeric – for entering English letters and symbols.
  • Amharic – for entering Amharic characters.

The cursor icon at the bottom of the screen shows which mode you are in:

Icon Mode
curser Numeric
curser Alphanumeric (lowercase)
curser Alphanumeric (uppercase)
curser Amharic

Numeric Mode (Default)

Use this mode for entering numbers, prices, and quantities.

Entering Numbers

  • Press the key that corresponds to the number you want.
  • The keys are labelled with numbers 1–9 and 0.

Entering Decimals

  • To enter a decimal point (.), press the key 6 twice until . appears.
  • You can only enter one decimal point.

Comma Formatting

  • Large numbers are automatically formatted with commas (e.g., 10,000).

Alphanumeric Mode

Use this mode for entering text (English), item names, customer names, and email addresses.

Entering Letters

Each key has multiple letters. Press the key repeatedly to cycle through the letters.

Key Letters
1 1 . @ ? ! * # % + - : " / |
2 a b c 2
3 d e f 3
4 g h i 4
5 j k l 5
6 m n o 6
7 p q r s 7
8 t u v 8
9 w x y z 9
0 space 0 _

Example: Typing "Apple"

  1. Press key 7 twice to get a.
  2. Press key 12 three times to get p.
  3. Press key 12 three times again to get p.
  4. Press key 10 three times to get l.
  5. Press key 8 twice to get e.

Caps Lock

  • Press the Function key (button 9) briefly to toggle Caps Lock on and off.
  • When Caps Lock is on, the cursor icon shows A (uppercase).

Special Characters

  • Press key 6 repeatedly to cycle through special characters:
  • ., @, ,, ?, !, *, #, %, +, -, :, ", /

Amharic Mode

Use this mode for entering Amharic text, customer names, and addresses.

Entering Amharic Characters

Each key has a base character. Press the key repeatedly to cycle through the derivatives.

Key Base Characters
2 ሀ ለ መ
3 ረ ሰ ሸ ቀ
4 በ ተ ቸ ነ
5 ኘ አ ከ
6 ወ ዘ ዠ
7 የ ደ ጀ ገ
8 ጠ ጨ ጰ
9 ፀ ፈ ፐ ቨ
0 space _ ፩ ፲ ፻ ፼

Amharic Character Families

When you select an Amharic base character, you can use the left (8) and right (6) keys to cycle through its family members.

For example, if you type , you can press right (6) to change it to , , , , , , .

  • Press middle key (7) to confirm the character.
  • Press backspace (5) to cancel and return to the previous character.

Example: Typing "ሰላም"

  1. Press key 3 twice to get .
  2. Press key 2 twice to get then press right and left key to choose from the members of eg navigate to then press enter
  3. Press key 2 three times to get then press right and left key to choose from the members of eg navigate to then press enter.

Editing Text

Action How to Do It
Delete last character Press Backspace (5).
Delete entire entry Press and hold Backspace (5).
Exit any input screen Press and hold Left (8).

Using Shortcuts

When entering data:

  • Press Function (9) then a number to access special functions (e.g., discount, new amount).
  • In menus, press Function (9) then a number to jump directly to a menu item.

Keypad Tips

  • Same key cycling – press the same key repeatedly to cycle through its characters.
  • Long press – hold a key for a special action (e.g., backspace clears all).
  • Cursor icon – shows which keypad mode you are in.
  • Max characters – the input box turns green when you reach the maximum allowed characters.

Next Steps

Learn how to read NFC cards.

➡️ Continue to Reading Cards