Skip to content

የግንኙነት ችግሮች

ይህ መመሪያ በእርስዎ ውሪ ነካ ላይ የሚያጋጥሙ የኔትወርክ ግንኙነት ችግሮችን ለመለየትና ለመፍታት ይረዳዎታል።


የኔትወርክ ሁኔታን መፈተሽ

በማስተካከያ (Settings) ስክሪን አናት ላይ የሚገኘው የሁኔታ ባር (status bar) የእርስዎን የኔትወርክ ግንኙነቶች ያሳያል (በስተግራ በኩል ያሉ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ምልክቶች)።

  • የውሪ ነካ በዋይፋይ (WiFi) እና በ ተሌኮም ዳታ (GPRS) ይሠራል።
  • የተመረጠው ሁነታ ዋይፋይ (WiFi) ከሆነ፣ የዋይፋይ ምልክቱ በስተግራ ጥግ ላይ ይቀመጣል፤ የGPRS ምልክቱ ደግሞ ይከተለዋል።
  • የተመረጠው ሁነታ GPRS ከሆነ፣ የGPRS ምልክቱ በስተግራ ጥግ ላይ ይቀመጣል፤ የዋይፋይ ምልክቱ ደግሞ ይከተለዋል።
ምልክት (Icon) ትርጉም
gprs ጥሩ የኔትወርክ ምልክት/ሲግናል (GPRS)
gprs ደካማ የኔትወርክ ምልክት/ሲግናል (GPRS)።
gprs በጣም ደካማ የኔትወርክ ምልክት/ሲግናል (GPRS)።
gprs ምንም የኔትወርክ ምልክት/ሲግናል የለም (GPRS)።
wifi ዋይፋይ (WiFi) በርቷል።
wifi ዋይፋይ (WiFi) ጠፍቷል።

የዋይፋይ ግንኙነት ችግሮች

መሣሪያው የዋይፋይ ኔትወርክን ማግኘት ካልቻለ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • በራውተሩ (router) ላይ ዋይፋይ ጠፍቷል።
  • መሣሪያው ከራውተሩ የሲግናል ክልል ውጪ ነው።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ራውተሩ መብራቱን እና ሲግናል እያሰራጨ መሆኑን ያረጋግጡ።
  2. ማሽኑን ወደ ራውተሩ አስጠግተው ያስቀምጡት።
  3. ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) > ዋይፋይ (WiFi) ውስጥ የኔትወርክ ስሙን (SSID) እና የይለፍ ቃሉን (PASSWORD) ያረጋግጡ።
  4. የኔትወርኩን ስም (SSID) እንደገና ለማስገባት ይሞክሩ።

ዋይፋይ አልገናኝ ካለ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • የተሳሳተ የይለፍ ቃል (password)።
  • ራውተሩ በጣም የራቀ መሆኑ።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) > ዋይፋይ (WiFi) ውስጥ የዋይፋይ ይለፍ ቃሉን እንደገና ያስገቡ።
  2. የይለፍ ቃሉ ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ (የእንግሊዘኛ በትልልቅ እና በትንንሽ ፊደላት መጻፉን ልብ ይበሉ)።
  3. ራውተሩ የ WPA2 ወይም የ WPA ደኅንነት ጥበቃ (security) እንደሚጠቀም ያረጋግጡ (መሣሪያው እነዚህን የደኅንነት ዓይነቶች ይደግፋል)።
  4. ራውተሩን እና ማሽኑን አጥፍተው ያብሩ (Restart ያድርጉ)።

ዋይፋይ እየተቆራረጠ ካስቸገረ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • የሲግናል መዳከም።
  • ከሌሎች መሣሪያዎች የሚመጣ የሞገድ ጣልቃ-ገብነት (interference)።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ማሽኑን ወደ ራውተሩ አስጠግተው ይያዙት።
  2. ማሽኑን ከብረት ዕቃዎች ወይም ከሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች አጠገብ አለማስቀመጥ።
  3. የዋይፋይ ግንኙነቱ የማይታመን ከሆነ ወደ GPRS ሁነታ ይቀይሩ።

የGPRS ግንኙነት ችግሮች

ምንም የሲግናል ምልክት ከሌለ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • መሣሪያው የኔትወርክ ሽፋን ደካማ በሆነበት አካባቢ መገኘቱ።

ምን መደረግ አለበት?

  1. የተሻለ የኔትወርክ ሽፋን ወዳለበት ቦታ ይንቀሳቀሱ።
  2. ወደ ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) > GPRS በመሄድ የGPRS ሁኔታን ይፈትሹ።
  3. ማሽኑን አጥፍተው ያብሩት።

"Network Not Found" (ኔትወርክ አልተገኘም) የሚል መልእክት ካሳየ

ምን መደረግ አለበት?

  1. ማሽኑን አጥፍተው ያብሩት (Restart ያድርጉት)።
  2. ወደ ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) > GPRS በመሄድ የGPRS ሁኔታን ይፈትሹ።
  3. ችግሩ አሁንም ካልተቀረፈ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ።

የመረጃ ልውውጥ ፍጥነት በጣም ቀርፋፋ ከሆነ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • የሲግናል መዳከም።
  • የኔትወርክ መጨናነቅ (congestion)።

ምን መደረግ አለበት?

  1. የተሻለ የሲግናል ጥራት ወዳለበት ቦታ ይንቀሳቀሱ።
  2. በምትኩ በዋይፋይ (WiFi) ለማገናኘት ይሞክሩ።
  3. ከተቻለ በአካባቢዎ ያለውን የኔትወርክ ሽፋን ሁኔታ ያረጋግጡ።

አጠቃላይ የግንኙነት ችግሮች

"No Response" (ምላሽ የለም) የሚል መልእክት ካሳየ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • ሲስተሙን (ማዕከላዊ ስርዓቱን) ማግኘት አልተቻለም።
  • ማሽኑ ከኔትወርክ ጋር አልተገናኘም።

ምን መደረግ አለበት?

  1. የኔትወርክ ግንኙነቱን (ዋይፋይ ወይም GPRS) ይፈትሹ።
  2. ማሽኑን አጥፍተው ያብሩት (Restart ያድርጉት)።
  3. የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ – ዋናው ሲስተም ሥራ አቁሞ (down ሆኖ) ሊሆን ይችላል።

"Please change to Wifi Mode" (እባክዎ ወደ ዋይፋይ ሁነታ ይቀይሩ) የሚል መልእክት ካሳየ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • ዋናው ሲስተም በGPRS ሊተላለፍ የማይችል በጣም ትልቅ መጠን ያለው ጥያቄ ልኳል።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) > ዋይፋይ (WiFi) ውስጥ ወደ ዋይፋይ ሁነታ ይቀይሩ።
  2. ማከናወን የፈለጉትን ተግባር ያጠናቅቁ።
  3. ተግባሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ GPRS መመለስ ይችላሉ።

"Time Server Error" (የሰዓት ሰርቨር ስህተት) የሚል መልእክት ካሳየ

ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች፦

  • መሣሪያው ትክክለኛውን ሰዓት ከኔትወርክ ማግኘት አልቻለም።

ምን መደረግ አለበት?

  1. ማሽኑን አጥፍተው ያብሩት (Restart ያድርጉት)።
  2. የኔትወርክ ግንኙነቱን ይፈትሹ።
  3. ችግሩ ከቀጠለ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ።

የኔትወርክ ምልክቱ ላይ የስህተት ምልክት ካለ (ባለአንድ ታወር ከቀይ X ምልክት ጋር)

ትርጉሙ፦

  • መሣሪያው ከማንኛውም ኔትወርክ ጋር አልተገናኘም።

ምን መደረግ አለበት?

  1. የተሻለ የሲግናል ጥራት ወዳለበት ቦታ ይንቀሳቀሱ።
  2. ወደ ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) ይሂዱ።
  3. እንደገና ለመገናኘት ዋይፋይ (WiFi) ወይም GPRS ን ይምረጡ።
  4. እንደገና መገናኘት ካልተቻለ ማሽኑን አጥፍተው ያብሩት።

ግንኙነትዎን መፈተሽ

መሣሪያው ከኔትወርክ ጋር በትክክል መገናኘቱን ለመፈተሽ፦

  1. ወደ ማስተካከያ (Settings) > ኔትወርክ (Network) ይሂዱ።
  2. የዋይፋይ ምልክቱን (WIFI ICON) ወይም የGPRS ምልክቱን (GPRS ICON) ይምረጡ።
  3. መሣሪያው በስክሪኑ ላይ "ኔትዎርክ ጋር ተገናኝቷ" የሚል አረንጓዴ መልእክት ካሳየ ግንኙነቱ በትክክል እየሠራ ነው፤ ካልሆነ ግን ማሽኑን አጥፍተው ያብሩት (Restart ያድርጉት)።

አሁንም ችግሮች ካጋጠሙዎት?

ከላይ የተጠቀሱትን እርምጃዎች በሙሉ ሞክረው ችግሩ ካልተቀረፈ፣ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ፦

  • ኢሜይል፦ info@adcethiopia.com
  • ስልክ፦ +251 93 007 6905

እባክዎ የመሣሪያዎን መለያ (Device ID) አስቀድመው ያዘጋጁ (በ ማስተካከያ [Settings] > የመሣሪያ መረጃ [Device Info] ውስጥ ይገኛል)።


የሚቀጥሉ እርምጃዎች

ወደ ሌሎች የዕክሎች መፍቻ መመሪያዎች ይቀጥሉ።

➡️ ወደ የሃርድዌር ችግሮች ይቀጥሉ

Connection Problems

This guide helps you diagnose and fix network connectivity issues on your Wurii NEKA.


Checking Your Network Status

The status bar at the top of the settings screen shows your network connections (left two icons)

  • The Wurii Neka works with wifi and gprs.
  • If WIFI is currently the selected mode, the WIFI icon will be on the left corener and the GPRS icon will follow
  • If GPRS is currently the selected mode, the GPRS icon will be on the left corener and the WIFI icon will follow
Icon Meaning
gprs Good network signal (GPRS).
gprs Weak signal (GPRS).
gprs No signal (GPRS).
gprs No signal (GPRS)
wifi Wifi is turned on.
wifi Wifi is off.

WiFi Connection Problems

Device Can't Find WiFi Network

Possible Causes:

  • WiFi is turned off on the router.
  • The device is out of range.

What to Do:

  1. Make sure the router is on and broadcasting.
  2. Move the device closer to the router.
  3. Check the SSID and PASSWORD in Settings > Network > WiFi.
  4. Try entering the SSID again.

WiFi Won't Connect

Possible Causes:

  • Incorrect password.
  • The router is too far.

What to Do:

  1. Re-enter the WiFi password in Settings > Network > WiFi.
  2. Make sure the password is correct (case‑sensitive).
  3. Check that the router uses WPA2 or WPA security (the device supports these).
  4. Restart the router and the device.

WiFi Keeps Disconnecting

Possible Causes:

  • Weak signal.
  • Interference from other devices.

What to Do:

  1. Move the device closer to the router.
  2. Avoid placing the device near metal objects or other electronics.
  3. Switch to GPRS if WiFi is unreliable.

GPRS Connection Problems

No Signal

Possible Causes:

  • The device is in an area with poor coverage.

What to Do:

  1. Move to an area with better coverage.
  2. Check gprs by going in Settings > Network > GPRS.
  3. Restart the device.

"Network Not Found" Message

What to Do:

  1. Restart the device.
  2. Check gprs by going in Settings > Network > GPRS.
  3. Go to Settings > Network > GPRS and try to connect manually.
  4. If the problem persists, contact support.

Slow Data Speed

Possible Causes:

  • Weak signal.
  • Network congestion.

What to Do:

  1. Move to an area with better signal.
  2. Try connecting via WiFi instead.
  3. If possible, check the network coverage in your area.

General Connection Issues

"No Response" Message

Possible Causes:

  • The system is not reachable.
  • The device is not connected to the network.

What to Do:

  1. Check the network connection (WiFi or GPRS).
  2. Restart the device.
  3. Contact support – the system may be down.

"Please change to Wifi Mode" Message

Possible Causes:

  • The system sent a request that is too large for GPRS.

What to Do:

  1. Switch to WiFi mode in Settings > Network > WiFi.
  2. Complete the operation.
  3. You can switch back to GPRS after.

"Time Server Error" Message

Possible Causes:

  • The device cannot get the correct time from the network.

What to Do:

  1. Restart the device.
  2. Check network connection.
  3. If the problem persists, contact support.

Network Icon Shows Error (single tower with Red X)

What It Means:

  • The device is not connected to any network.

What to Do:

  1. Go to Settings > Network.
  2. Select WiFi or GPRS to reconnect.
  3. If reconnecting fails, restart the device.

Testing Your Connection

To test if the device is connected:

  1. Go to Settings > Network.
  2. Select WIFI ICON or GPRS ICON.
  3. If the device shows on the screen "Connectd to Network" in green, the connection is working otherwise restart the device.

Still Having Problems?

If you have tried all the steps above and the issue persists, contact support:

  • Email: info@adcethiopia.com
  • Phone: +251 93 007 6905

Please have your Device ID ready (found in Settings > Device Info).


Next Steps

Continue to other troubleshooting guides.

➡️ Continue to Hardware Issues